የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ሕብረት::

 በሃገር ውስጥ ያሉ ወጣቶችና እና በውጪው ዓለማት የሚገኙ ወጣት ዳያስፖራዎችን በአንድነት በመቀናጀት የሚሰራ ሲሆን ዋና ዓላማው:: 

  • 1ኛ) በውጪው ዓለማት ተወልደው ያደጉ ወይም ልጅ እያሉ የመጡትን ወጣቶች  ሃገር ውስጥ ካሉ ወጣቶች ጋር በሶሻል ሚዲያም ሆነ በአካል በማገናኘት ስለ ሃገራቸው ባሕልና ታሪክ ቋንቋ እርስ በእርስ እንዲማማሩ ማድረግ::

  • 2ኛ) የተለያየ እውቀት ያላቸው ከሃገር ውስጥ ሆነ ከውጪው ዓለማት የሚገኙ ሙሁራኖችን በመጋበዝ በተለያዩ ፕላት ፎርም ወጣቱ እንዲማርና እንዲለወጥ  ማድረግ::

  • 3ኛ)በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን እያንዳንዱ ወጣት ስለ ሃገሬ ያገባኛል በማለት የዲፕሎማሲና አድቮከሲ ወታደር የመረጃ ጦረኛ እንዲሆን እንዲሰሩ ማስተማር እና ማሰማራት:: ይህንንም የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ወጣቶች ሕብረት አደረጃጀት መሬት ወርዶ ሚስራበትና ሚተገበርበትን መንገድ ማመቻቸት ነው::

  • 4ኛ) በሃገር ውስጥም በውጪ ዓለማት የሚገኙትን ወጣቶች በማቀናጀት በሶሻል ሚዲያ ማለትም በዋናነት በቲውተር ካምፔን ላይ ተሳትፎ በማረግ የሃገራችንን መልካም ገፀታ ለዓለሙ ማህበረሰ ማሳወቅ ሌላው ትልቁ ሚሰራበት ስራ ነው::

  • 5ኛ) በሃገር ውስጥ ያሉ ስራ አጥ የሆኑትን ወጣቶች የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠትና በማስተማር ወደ ተለያየ የስራ ዘርፍ እንዲሰማራ ማድረግ:: ከዚያም ባለፈ በውጪው ዓለማት የሚገኘው ወጣቶች በሃገር ውስጥ ያሉትን ወጣቶች በሚያስፈልጋቸው በእውቀትና በገንዘብ እናም በተለያዩ ቁሳቁስ እርዳታን በማረግ ሃገራቸውን እንዲቀይሩ ማድረግ ነው:: 

  • 6ኛ) በቱሪዝሙ አቅጣጫ በውጭ ዓለማት ያሉ ውጣቶች  ስለ ሃገራቸው መልካም  የተፈጥሮ ፀጋና ገፅታ ለዓለም ማህበረሰብ በማሰወቅ የውጪው ዓለም ማህበረሰብ ወደ ሃገር ውስጥ እንዲመጣ ማነሳሳትና በሃገር ውስጥ ያለው ወጣቶችም ለቱሪዝም ሚመጡትን በማስጎብኝት እና በማሳየት የቱሪዝሙን እድገት ከፍ እንዲል ማድረግ ነው::